Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
እሰጥሃለሁ ሕይወቴን — ጆይፉል ሳውንድ

እሰጥሃለሁ ሕይወቴን እሰጥሃለሁ ዘመኔን

እሰጥሃለሁ ዕድሜዬን ለአንተ ለአምላኬ

ሳልሰጥህ የኔ ብዬ የማስቀረው ምንም የለኝ

ነፍሴን መንፈሴን ስጋዬን አስረክባለሁኝ

በእጆቼ ሰርቼ የማገኘውን ገንዘቤን

በጥረት ያገኘሁት ዕውቀቴን

በተፈጥሮ የተሰጠኝ ችሎታዬን

እንካ ውሰደው እሰጥሃለሁ ለአንተ ለጌታዬ