Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወዶኛል

Wedognal

2004 · ትራክ 1 · 3:57 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዙፋኑን ትቶ ወረደ

ፈልጐ እኔን ሊያገኘኝ

ሳልወደው ቀድሞ ወደደኝ

ከዓለም ለይቶ መረጠኝ

በውርደት ሞትን ከመሞት

ፍቅሩን ለእኔ ገለጠልኝ

ከዘለዓለም ፍቅር ስቦ

ወደ እልፍኙ አስገባኝ

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ከእልፍ የተመረጠ ነው

ፍቅሩ ለዘላዓለም ነው

ወዶኛል ወድጄዋለሁ

እንደርሱ የታለ ማነው (፪x)

ማንም መጥቶ አይነጥለኝ

አንዴ የእራሱ አድርጐኛል

ይተወኛል ብዬ አልፈራም

የከሳሼን ወሬ አልሰማም

ወረተኛ አይደል እንደሰው ለዘለዓለም ወዶኛል

ጥፋት እንኳን ሲያገኝብኝ በፍቅር መክሮ ያድነኛል

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ከእልፍ የተመረጠ ነው

ፍቅሩ ለዘላዓለም ነው

ወዶኛል ወድጄዋለሁ

እንደርሱ የታለ ማነው (፪x)

ግርማው በቃል አይገለጽ

ፊቱ እንደፀሐይ ሲያበራ

ከእኔ ወዳጅ አይበልጥም

ማንም በምንም ቢጠራ

በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል

ሁልጊዜ ሃሴት አደርጋለሁ

ኩራት ኩራት ይሰማኛል

የእርሱ መሆኔ አርክቶኛል

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ከእልፍ የተመረጠ ነው

ፍቅሩ ለዘላዓለም ነው

ወዶኛል ወድጄዋለሁ

እንደርሱ የታለ ማነው (፪x)

ይታወቅ በምድር ሁሉ

እኔ ኢየሱስን መውደዴ

ያኮራል ያስመካል እንጂ

አያሳፍረኝም ውዴ

ከእርሱ ጋር የምሆንበት

የሠርጌን ቀን ናፍቄያለሁ

ነፍሴን በደሙ አንጽቼ

ምጻቱን እጠብቃለሁ

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ከእልፍ የተመረጠ ነው

ፍቅሩ ለዘላዓለም ነው

ወዶኛል ወድጄዋለሁ

እንደርሱ የታለ ማነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ