Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ወለል ያለ — ኢየሩሳሌም ነጊያ

ወገግታዬ ነው የማለዳ ጮራዬ

ከእርሱ የተነሳ በራ ጨለማዬ

ጣዕመ ቢስ ልሳኔን አንደበቴን በራ

ሕይወቴ ጨፍጋጋ እንዳይሆን መራራ

አመዴን አራግፎ ወዛም ያደረገኝ

በሰዎች ሁሉ ፊት በሞገስ አቆመኝ