Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ዉዴ — ሐምሌት በልጁን

ስለኔ ሀጥያት የሞተልኝ

ነፍሱን አሳልፎ የሰጠኝ

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር

ከቶ ለማንም የለም

ነፍሱን በፈቃዱ የሰጠ ለአዳም ዘር

ወደ ምድር መጣ ቤዛ ሊሆን ለአለም

ዘወትር በአብ ፊት ስለ እኛ ሚማልደው

የአዲስ ኪዳን ዋስ እየሱስ ፍቅሩ ማያረጀው