Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ይሄ ነው — አዜብ ኃይሉ

እጅጉን ሲራራ በብዙ ሲምር

ከቶ ያበቃለትን የሞት ፍርድ ሲሽር

ሲስብ ወደራሱ ለክብር መንግስቱ

እኔ እርሱን የማውቀው በሰፊ ትዕግስቱ

መክሮ ሲመልስ ለክብር ሲያበቃ

ውጦ ከሚያስቀር ከረግረጉ ጭቃ

ታሪክ ቀይሮ ሥምንም ሲለውጥ

ነጥቆም ሲታደግ ካንሸራታቹ ድጥ (፪x)