የከበረ
Yekebere
2012 · ትራክ 7 · 5:57 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የከበረ ከሁሉ የተሻለ (፪x)
ሰውነቴን ለአንተ አቀርባለሁ (፪x)
እኔነቴን ለአንተ አቀርባለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መሰዊያን ሰራሁኝ
ልሰዋልህ በፊትህ ላቀርበው
ያለኝን በሙሉ ታውቀዋለህ
የቱን ነው ምትሻው
እያልኩኝ ስደረድር
ምድርና ሞላዋ
ለካስ የአንተ ነው
የሚቃጠል መስዋዕት
ደስ እንዳያሰኝህ
ይህንን ተረዳሁ
ታዲያ እኔ ምኔን ልስጥህ
ምኔን ሰጥቼ/ሰውቼ ደስ ላሰኝህ
እያልኩኝ ስጠይቅ ቃልህን
አዝማች · Chorus
ስጠው/ሰዋው አለኝ እራስህን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለዚህ እራሴን
ሕያውና ቅዱስ አድርጌ
ፊትህን ደስ እንዳሰኘው
ፈቀድኩኝ ልሰዋ ይኸው
ልዩ ጣዕም የመዓዛ ሽታ
ሆኜ ልቅረብ በፊትህ ጌታ
ከሚቃጠል መስዋዕት ጋራ ወደፊትህ እመጣለሁ ኦሆሆ ኦሆሆ ሆሆ
የአምልኮዬ መዓዛ ሽታ ዙፋንህን ይክበበው ኦሆሆ ኦሆሆ ሆሆ
በምህረት የተሞላህ ታላቅ አምላክ ነህና ኦሆሆ
ቁጥር 3 · Verse 3
አሁንም አበዛለሁ ከነፍሴ ምሥጋና
ኦ በምሥጋና
በዝማሬ እመጣለሁ
ኦሆሆ ወደ ማደሪያህ እገባለሁ (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ