Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
የሚረዳኝ — ኢየሩሳሌም ነጊያ

ፀሐይ አሽቆልቁላ በምዕራብ ስትጠልቅ

ለምሽት ተረኛ ለጨረቃ ስትለቅ

ጐኔን ላሳርፈው ከቀኑ ድካሜ

ስተኛ እንቅልፌ ሲያደርሰኝ ከህልሜ

ህልሜ ቅዥእት ሆኖ ጨለማው በርትቶ

እጥፍ ሲሆን ሌቱ ሲረዝም ምሽቱ

አቤቱ ወደአንተ ድምጼን አሰማለሁ

ፈጥነህ እንደትመጣ እለምንሃለሁ