Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
የዛሬ ቤተክርስቲያን — ደረጀ ከበደ

በቀድሞው ስብስብ በአዲስ ኪዳን ህብረት

ምዕመናን አብረው በተከማቹበት

ንብረቱን ገንዘቡን ሁሉን እያመጣ

ማንም ሳይራቆት እንጀራም ሳያጣ

በአንድ ልብ ጌታን እያመሰገኑ

ይቆርሱ ነበረ ያኔ ምዕመኑ