Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ይመጣል — ዳዊት ጌታቸው

እንዴት እንሆን ይሆን ፊትለፊት ስናየው

ያዘጋጀነውን ጥያቄ ትተነው

ፈዘን በውበቱ በሚያስደንቅ ግርማው

አይን አይኑን እያየን እሱን ማወደስ ነው

ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር

ሊወስደን እንድንኖር ከእርሱ ጋር

ተስፋችን ኢየሱስ በሀይል ይገለጣል

የወጉትም ደግሞ በአይናቸው ያዩታል