Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች
ዘንበል አለልኝ — ተፈራ ነጋሽ

እግዚአብሔርን ቆይቼ ደጅ ጠናሁት

ሁሉ በእርሱ እንደሚሆን ስላመንኩት

እርሱም ጩኸቴን ሰምቶ አዘነልኝ

ዘንበል አለልኝ ወደኔ ዘንበል አለልኝ (፪x)

ከረግረጉ ጭቃ ከጥፋትም ጉድጓድ

ከአስፈሪው ጨለማ ከሰይጣንም ወጥመድ

አስመለጠን ጌታ በዛ ቸርነቱ

ምርኮዬም ተመለሰ አበራልኝ ፊቱ