Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አዲስ ዘመን

Adis Zemen

2017 · ትራክ 1 · 4:35 · አማርኛ · የተስፋ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያለፈው አለፈ አዲስ ተጀመረ

ጨለማው ተገፍፎ ብርሃን ፈነጠቀ

ያዘንኩበት ሌሊት ተፈጸመና

የደስታ ማለዳ መጣልኝ እነሆ

አዲስ ዘመን ሰጠኸኝ

አዲስ መዝሙር በአፌ

የቀደመው ትዝ አይለኝም

አዲስ ነገር አደረግህልኝ

በምድረ በዳው መንገድ ሠራህ

በበረሃው ወንዝ አፈሰስህ

የደረቀው ሁሉ ለመለመ

የሞተው ተስፋዬ ተነሳ

አዲስ ዘመን ሰጠኸኝ

አዲስ መዝሙር በአፌ

የቀደመው ትዝ አይለኝም

አዲስ ነገር አደረግህልኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ