Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስለሆነ ስላንተ

Silehone Silante

2017 · ትራክ 2 · 5:01 · አማርኛ · ምስጋና

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ማን ነበርኩ እኔ ብትዘክረኝ

ከአፈር ያነሳኸኝ ከጉድጓድ

ስምህን እንድጠራ ማን አበቃኝ

ጸጋህ ነው ይህ ሁሉ ጸጋህ

ስለሆነ ስላንተ እዘምራለሁ

ስለቸርነትህ እመሰክራለሁ

ዘመኔ ሁሉ ቢያልቅ በምስጋና

ውለታህን መቁጠር አልጨርስም

ትናንት የደከመው ዛሬ በረታ

ትናንት ያለቀሰው ዛሬ ዘመረ

ይህ የአንተ ሥራ ነው በሕይወቴ

ድንቅ ነው በዓይኔ ፊት የማየው

ስለሆነ ስላንተ እዘምራለሁ

ስለቸርነትህ እመሰክራለሁ

ዘመኔ ሁሉ ቢያልቅ በምስጋና

ውለታህን መቁጠር አልጨርስም

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ