Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልረሳም

Alresam

2003 · ትራክ 4 · 4:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አልረሳም አልረሳም አልረሳም

የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን

ጌታ የባረከኝን

ከ ትቢያ ያነሳኝን

እንዴት እረሳለሁ

አስታውሰዋለሁ

እንዴት እረሳለሁ

ጌታን አከብራለሁ

ዙሪያው ገደል ሆኖ መውጫ አጥቼ

ከምስጋና ህይወት ተለይቼ

ግን እግዚአብሔር በጣም አዘነ

እንደገና አቆመኝ በአዲስ ጉልበት

አልረሳም አልረሳም አልረሳም

የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን

ጌታ የባረከኝን

ከ ትቢያ ያነሳኝን

እንዴት እረሳለሁ

አስታውሰዋለሁ

እንዴት እረሳለሁ

ጌታን አከብራለሁ

ነፍሴን እጅግ ተርባ ተጠምታብኝ

ቀኑ እንደ እረፍት ሲሆንብኝ

የሰማይን መስኮት ከፈተና

ጓዳዬን ሞላልኝ በምስጋና

አልረሳም አልረሳም አልረሳም

የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን

ጌታ የባረከኝን

ከ ትቢያ ያነሳኝን

እንዴት እረሳለሁ

አስታውሰዋለሁ

እንዴት እረሳለሁ

ጌታን አከብራለሁ

የመከራው ሌሊት ምንው በዛ

እግዚአብሔር ዝም አለኝ እንደዋዛ

ብዬ ነበር ግን ጌታ አይጥልም

ሰምቶ ይመልሳል ዝም አይልም

አልረሳም አልረሳም አልረሳም

የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን

ጌታ የባረከኝን

ከ ትቢያ ያነሳኝን

እንዴት እረሳለሁ

አስታውሰዋለሁ

እንዴት እረሳለሁ

ጌታን አከብራለሁ

ዕሰይ ሜዳ ሆነ ያ ተራራ

ሌሊቱ አልፎ ጨለማዬ በራ

የረዳኝም ጌታ እባርከዋለሁ

በጉባኤ መሃል አዜምለታለሁ

አልረሳም አልረሳም አልረሳም

የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን

ጌታ የባረከኝን

ከ ትቢያ ያነሳኝን

እንዴት እረሳለሁ

አስታውሰዋለሁ

እንዴት እረሳለሁ

ጌታን አከብራለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ