አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል
Anten Kagenye Sew Men Yehonal
2002 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ
እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (2x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አባትስ ማለት እንደ አንተ ነው
ወዳጅስ ማለት እንደ አንተ ነው
አሳድገኽኛል ከእጅህ እየበላሁ
ሰው የሆንኩት በአንተ ነው
ይህንን ልቤ አልረሳው (4x)
አዝማች · Chorus
አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል (2x)
አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል (2x)
የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ
እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (2x)
ዘመን ሲከፋ ሲቀያየር
አንተ ግን ያው ነህ እግዚአብሔር
ፀጋህ አልጐደለ ለእኔ ለልጅህ
ቤትህ ያገባኛል አባብሎ ምህረትህ (4x)
አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ
እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (2x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አትለዋወጥ ጠዋት ማታ
ፊትህ አይጠቁር የእኔ ጌታ
አልቆረቆረኝም ትከሻህ ጌታዬ
ተመችተኽኛል አንተ ነህ አለኝታዬ (4x)
አዝማች · Chorus
አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ
እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (2x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰማይ ምድርንም ትገዛለህ
የፈቀድከውን ታደርጋለህ
አንዳች አላጣሁም በስምህ ለምኜ
ፊቴ አላፈረም እጅህን ታምኜ (4x)
አዝማች · Chorus
አንተን ከአገኘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
አንተን ከያዘ ሰው ምን ይሆናል አሃሃ (2x)
የልቤ ማረፊያ ነህ የማምለጫ አለቴ
እኮራብሃለሁኝ ኢየሱስ መድሃኒቴ (2x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ