ምህረትህ
Mehereteh
2002 · ትራክ 7 · 7:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተ ከወደድከኝ የሚጠላኝ ማነው (፪x)
አንተ ካጸደከኝ የሚከሰኝ ማነው (፪x)
አንተ ከወደድከኝ የሚጠላኝ ማነው (፪x)
አንተ ካጸደከኝ የሚከሰኝ ማነው (፪x)
ማነው ፣ ማነው (፫x)
ስሙን አከብራለሁ ይህን ጌታ
ቀንበሬን ሰባብሮ እኔን ፈታ (፪x)
ኀጢአቴም ተሻረ ተወገዷል
ምህረቱን በእኔ ላይ አግኖታል (፪x)
አሃሃሃሃሃ ምህረቱ ለእኔ ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህ በዝቶልኝ ነው መኖሬ (፫x)
እጅህ ስለያዘኝ ነው መኖሬ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምህረትህ በዝቶልኝ ነው መኖሬ (፫x)
እጅህ ስለያዘኝ ነው መኖሬ (፫x)
ጠላቴን ከእግሬ ስር ጥሎልኛል
እግዚአብሔር ሞገሴ ሆኖልኛል (፪x)
ድንቁን አወራለሁ በዘመኔ
ድጋፌ ነው ጌታ መድህኔ (፪x)
አሃሃሃሃሃ ምህረቱ ለእኔ ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህ በዝቶልኝ ነው መኖሬ (፫x)
እጅህ ስለያዘኝ ነው መኖሬ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አባት ስለሆንከኝ ነው መኖሬ (፫x)
እጅህ ስለያዘኝ ነው መኖሬ (፫x)
ምድርና ሞላዋ የእግዚአብሔር ናት
ዓለምን በፍቅሩ የሚመራት (፪x)
ስለወደደንም አድኖናል
ማንም አይከሰንም አጽድቆናል (፪x)
አሃሃሃሃሃ ምህረቱ ለአንተ ነው (፬x)
አሃሃሃሃሃ ምህረቱ ለአንቺ ነው (፬x)
አሃሃሃሃሃ ምህረቱ ለእኛ ነው (፬x)
አሃሃሃሃሃ ምህረቱ ለእኔ ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህ በዝቶልኝ ነው መኖሬ (፫x)
እጅህ ስለያዘኝ ነው መኖሬ (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አባት ስለሆንከኝ ነው መኖሬ (፫x)
ምህረትህ ገኖልኝ ነው መኖሬ (፫x)
አንተ ከወደድከኝ የሚጠላኝ ማነው (፪x)
አንተ ካጸደከኝ የሚከሰኝ ማነው (፪x)
አንተ ከወደድከኝ የሚጠላኝ ማነው (፪x)
አንተ ካጸደከኝ የሚከሰኝ ማነው (፪x)
ማነው ፣ ማነው (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ