Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አጠገቤ ሆኗል

Ategebie Honual

2013 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አጠገቤ ሆኗል ጌታ (፬x)

ከእንግዲህ የቱ ያስፈራኛል

እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል

ከእንግዲህ የቱ ያሰጋኛል

አባቴ ቅጥር ሆኖልኛል

በብቸኝነቴ አይዞህ ባይ ማጣቴ

ትዝ ሲለኝ (፪x)

የለቅሶ እንጉርጉሮ ሲሰማ ከቤቴ

ትዝ ሲለኝ (፪x)

የእኔስ ነገር የእኔስ

በዓይን አይቶ ሳለቅስ

ያልራቀኝ ንጉሥ

የልጅነት ጓደኛ

ስሆን ያኔ ብቸኛ

ኢየሱስ አለኛ

አጠገቤ ሆኗል ጌታ (፬x)

ከእንግዲህ የቱ ያስፈራኛል

እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል

ከእንግዲህ የቱ ያሰጋኛል

አባቴ ቅጥር ሆኖልኛል

የቅርብ ወንድሞቼ ሁሉ የከዱኝ

ትዝ ሲለኝ (፪x)

ያለርህራሄ ጉድጓድ የጣሉኝ

ትዝ ሲለኝ (፪x)

የእኔስ ነገር የእኔስ

በዓይን አይቶ ሳለቅስ

ያልራቀኝ ንጉሥ

የልጅነት ጓደኛ

ስሆን ያኔ ብቸኛ

ኢየሱስ አለኛ

አጠገቤ ሆኗል ጌታ (፬x)

ከእንግዲህ የቱ ያስፈራኛል

እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል

ከእንግዲህ የቱ ያሰጋኛል

አባቴ ቅጥር ሆኖልኛል

ለእኔስ አይዞህ ብለው የሚያጽናኑኝ

ወዳጆቼም ችላ ቢሉኝ

የቅርቦቼም ችላ ቢሉኝ

እናት ልጇን እንኳን ብትረሳ

ልጄ ካለ የማይከዳ

ጌታ አለ ከእኔስ ጋራ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ