Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምልኮ አለኝ

Amleko Alegn

2013 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተስፋ የሌለውን ሰው ተስፈኛ ላደረከው

ክብር ላላወቀውም ክብር ላሳየከው (፪x)

አምልኮ አለኝ አምልኮ (፪x)

ዝማሬ አለኝ ዝማሬ (፪x)

አምልኮ አለኝ ዝማሬ አለኝ

ክብር አለኝ ስግደት አለኝ (፪x)

አምልኮ አለኝ አምልኮ (፪x)

ዝማሬ አለኝ ዝማሬ (፪x)

ግራ ቀኙ ሁሉ ተስፋ ሚያስቆርጥ ነው

የሚሰማው ነገር አንገት ሚያስደፋ ነው

ግን የጌታዬን ድምጽ ቀና ስል ስሰማ

ተስፋ አለህ አለኝ ጠላቴ እየሰማ

ተስፋዬ ጌታዬ እኮ ነው

በዝማሬ እስቲ ላክብረው (፪x)

ተስፋዬ ጌታዬ እኮ ነው

በሽብሸባ እስቲ ላክብረው (፪x)

ተስፋ የሌለውን ሰው ተስፈኛ ላደረከው

ክብር ላላወቀውም ክብር ላሳየከው (፪x)

አምልኮ አለኝ አምልኮ (፪x)

ዝማሬ አለኝ ዝማሬ (፪x)

ሁሉም በየፊናው በምርጫው ቢጓዝም

ከግብጽ ያወጣውን አምላኩን ባይመርጥም

በዘመን ፍጻሜ ከጌታ ሆነናል

በእኔና በእኔ ቤት ጌታ ይመለካል

አምልኮ አለኝ ዝማሬ አለኝ

ክብር አለኝ ስግደት አለኝ (፪x)

አምልኮ አለኝ አምልኮ (፪x)

ዝማሬ አለኝ ዝማሬ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ