Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አጽዳኝ

Atsidagn

2018 · ትራክ 2 · 5:18 · አማርኛ · የንስሐ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ

እንደ ምሕረትህ ብዛት ደምስስልኝ

መተላለፌን እኔ አውቃለሁ

ኃጢአቴ ሁልጊዜ በፊቴ ነው

አጽዳኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ

እጠበኝ ከኃጢአቴ ሁሉ

ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ አምላኬ

የቀና መንፈስ በውስጤ አድስ

ከፊትህ አትጣለኝ

ቅዱስ መንፈስህን አትውሰድብኝ

የደስታህን ስጦታ መልስልኝ

በበጎ ፈቃድህ ደግፈኝ

አጽዳኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ

እጠበኝ ከኃጢአቴ ሁሉ

ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ አምላኬ

የቀና መንፈስ በውስጤ አድስ

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ