ተመለስኩ
Temelesku
2018 · ትራክ 1 · 5:42 · አማርኛ · የንስሐ
ቁጥር 1 · Verse 1
ርቄ ሄጄ ነበር ከቤትህ ወጥቼ
የራሴን መንገድ መርጬ ተጓዝኩ
ያገኘሁት ግን ባዶነት ነበር
የአሳማ መኖ እንኳ ተከለከልኩ
አዝማች · Chorus
ተመለስኩ አባቴ ተመለስኩ
ይቅር በለኝ ብዬ መጣሁ
ልጅህ ልባል አይገባኝም
እንደ አንዱ ሞያተኛ ቁጠረኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ገና ሩቅ ሳለሁ አየኸኝ
ሮጠህ መጥተህ አቀፍከኝ
ካባ አለበስከኝ ቀለበት አጠለቅህልኝ
የሞተው ልጄ ተገኘ አልክ
አዝማች · Chorus
ተመለስኩ አባቴ ተመለስኩ
ይቅር በለኝ ብዬ መጣሁ
ልጅህ ልባል አይገባኝም
እንደ አንዱ ሞያተኛ ቁጠረኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ