Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ባልጠፋ ሰው

Baltefa Sew

2011 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባልጠፋ ሰው በእኔ አካል ውስጥ ገባህ

መኖርያ ለክብርህ ሰራህ ኣበጃህ

ስትገባ በውስጤ ሰው ሰው ሸተትኩኝ

ከሙቱ ከእኔ ሕይወት ሰላም ወጣኝ

ኃይሉ የሰው ቢሆን የአምላካችን የእግዚአብሔር

ከእኛ መካከል እነማን እንጠራ ነበር

እንዴት ይሆናል የእናንተን በእርግጥ ባላውቅም

በእኔ እይታ ግን ለአምላኬ መንግስት አይታሰብም

ምስኪን ምናምንቴ ለቁም ነገር ማልሆን

ፀጋ ቢስ ሌባ ሸክላ ነኝ ምሰበር

ከጠላቴ መቅሰፍት ስሸሽ አየኝና

ከሞት አተረፈኝ በውስጤ ገባና

ባልጠፋ ሰው በእኔ አካል ውስጥ ገባህ

መኖርያ ለክብርህ ሰራህ ኣበጃህ

ስትገባ በውስጤ ሰው ሰው ሸተትኩኝ

ከሙቱ ከእኔ ሕይወት ሰላም ወጣኝ

የሰው ሰው የተባሉ በጣም ባላቸው የከበሩ

እኔን ለምን ጠራኝ በምን ምክንያት እነሱ ቀሩ

እኔጃ ምክንያቱ በውል በቅጥ ባይገባኝም

እኔን ያስወደደው ፍቅሩ ነው ይህንን አልክድም

ፍቅር ሀይለኛ ነው ኃጢአት ያስሻረው

ይመስገን እየሱስ ህይዎቴ ከዚያ ነው

ባልጠፋ ሰው በእኔ አካል ውስጥ ገባህ

መኖርያ ለክብርህ ሰራህ ኣበጃህ

ስትገባ በውስጤ ሰው ሰው ሸተትኩኝ

ከሙቱ ከእኔ ሕይወት ሰላም ወጣኝ

አምላኬ እንዲገባ ውስጤን ለእሱ አላስዋብኩለት

መንገድ አላበጀው ቤቴንም አላጸደሁለት

በጠጠር በእሾህ ተራምዶ ነው ቤቴ የመጣው

ገረመኝ ፍቅሩ የታላቁ ንጉስ ትህትና

ሰባራ ቀዳዳውን ጠራርጎ ገባ

እረፍትን ሰጣኝ ሰላሜን አበዛ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ