እንውጣ ለወንጌል
Enwuta Lewongel
2011 · ትራክ 2 · 6:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክቡር ቅርሳቸውን ቀዬያቸውን ትተው
ቁልቁል ወረዱ ማዕረጋቸውን ጥለው
ነፍስ አወራርደው ለወንጌል እውነት
ወስነው ወጡ ሞትን ለመሞት
መኖርያ ዘመድ ሃገር እያላቸው
ለወንጌል ብለው አውሬ በላቸው
እንደተረገሙ ሰው ቆጥሯቸው
ለሃገር ሁሉ ጦስ አረጓቸው
አዝማች · Chorus
ታሪኩን ሰምተን ዝም አይደል
እንውጣ ለወንጌል እንጋደል
ለምን እንተኛለን የእግዜአብሄር ሰዎች
ሲጨምር ቁጥራቸው የምድር ሙታኖች
ለእኛም ተሰብኮ ነው የመጣነው
አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው
የአባቶቻችን አጥንት ይታዘበናል
ኧረ እያሱስ ምን ይለናል
ቁጥር 2 · Verse 2
ያለ ዳኛ ፍርድ ታርደው ተጣሉ
ክቡር ሰው ሲሆኑ ከእቃም ቀለሉ
ሰአትን ሳይመርጡ ያለመታከት
ሌሊቱን ከቀን የሚያገናኙ
ያለ እረፍት እንቅልፍ ከቀን እስከ ንጋት
በወህኒ ግርፋት የመከራው ስደት (፪x)
ረሃብ ዘመዳችው ጥማት ጓደኛቸው
ብርድና ውርጩ ውጭ አዳራቸው
የቀትሩ ፀሃይ የሀሩሩ ብዛት
ረዥሙ በረሃ የማይሻል ከሞት
አከሰላቸው መልካቸውን አጡ
ጤንነታቸውን ለወንጌል ተዉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ታሪኩን ሰምተን ዝም አይደል
እንውጣ ለወንጌል እንጋደል
ለምን እንተኛለን የእግዜአብሄር ሰዎች
ሲጨምር ቁጥራቸው የምድር ሙታኖች
ለእኛም ተሰብኮ ነው የመጣነው
አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው
የአባቶቻችን አጥንት ይታዘበናል
ኧረ እያሱስ ምን ይለናል
ቁጥር 3 · Verse 3
ለጌታ ቃል ብለው ከቤተሰባቸው
ከምወዱት ሃገር ከልጅ ከአባታቸው
ተለይተው ወጡ ጠፋ አድራሻቸው
ገደል ተራራ ስር ሆነ መኖርያቸው
ተባብረው ጠሏቸው ፍጥረታት ሁሉ
ቀባሪ ኣጡ በሜዳ ተጣሉ
ተሰነጠቁ ህይዎት እያላቸው
ያለፉት ሰማእታት አቤት ስቃያቸው
አዝማች · Chorus
ታሪኩን ሰምተን ዝም አይደል
እንውጣ ለወንጌል እንጋደል
ለምን እንተኛለን የእግዜአብሄር ሰዎች
ሲጨምር ቁጥራቸው የምድር ሙታኖች
ለእኛም ተሰብኮ ነው የመጣነው
አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው
የአባቶቻችን አጥንት ይታዘበናል
ኧረ እያሱስ ምን ይለናል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ