በፍቅሩ ይዞኛል
Befeqru Yezognal
2008 · ትራክ 2 · 6:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅሩ ይዞኛል በደግነቱ
ልዘምር በቃ ልቁም በፊቱ (፪x)
በፊቴ የሚቆም አይኑር ከልካይ
አይሆንልኝም እሱን (ፊቱን) ሳላይ (፪x)
ቀኑ አይገፋም እንዲህ እንደዋዛ
ከኢየሱስ ውጪ ምን አለው ለዛ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለካስ ሁሉም ከንቱ ነው
(እህም) የከንቱ ከንቱ ነው
አንተን መያዝ ግን ታላቅ ትርፍ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከጆችህ አምልጬ ወዴት እሄዳለው
ከአንተ ሌላ ኑሮ ምድረበዳ ነው (፪x)
ከአንተ ጋር መኖር እረፍት ነው
ከአንተ ጋር መኖር ሕይወት ነው (፪x)
አዝንክልኝ ጌታዪ እራራህልኝ
እጄን ላንሳ ልባርክህ ኦሆሆ ልባርክህ
ልነሳ ላነሳሳው እንጂ ፍቅርህን ጌታዬ
ሳላመልክ እንዴት እኖራለው ማምለክ ነውና ድርሻዬ
አዝማች · Chorus
ለካስ ሁሉም ከንቱ ነው
(እህም) የከንቱ ከንቱ ነው
አንተን መያዝ ግን ታላቅ ትርፍ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍቅሩ ይዞኛል በደግነቱ
ልዘምር በቃ ልቁም በፊቱ (፪x)
በፊቴ የሚቆም አይኑር ከልካይ
አይሆንልኝም እሱን (ፊቱን) ሳላይ (፪x)
ቀኑ አይገፋም እንዲህ እንደዋዛ
ከኢየሱስ ውጪ ምን አለው ለዛ (፪x)
አዝማች · Chorus
ለካስ ሁሉም ከንቱ ነው
(እህም) የከንቱ ከንቱ ነው
አንተን መያዝ ግን ታላቅ ትርፍ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ