በሞቱ አዳነኝ
Bemotu Adanegn
ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) እኔኑ ፍለጋ ፤ ዓመጸኛውን ሰው
ተዋረድክ ኢየሱስ ክብር ለሌለው
እኔኑ ከውርደት ከማጥ አወጣኸኝ
ተመስገን በልፋት በጣር መጥተህ
ኤሎሄ ላማሰበቅታኒ እስክትል የተሰቃየኸው
ስለእኔ ሞትህ ልታድነኝ በበዛው የመስቀል ጣርህ
ስለእኔ ለከፈልከው ዋጋ
መታሰቢያ ላድርግ እስኪ ዛሬ
ለመክፈል ዋጋ ካሣ ባይኖረኝም
ቁጥር 2 · Verse 2
ላክብርህ በፊትህ ዘምሬ (፪)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስኪ አስቡት ጌታን! አቤቱ!
ማንስ ይወድህ ዘንድ? ሃሌሉያ!
ማንም እንዲወድህ ደም ግባት የለህም
የሕማም ሰው ነበርክ ደዌ ያደቀቀህ
በመገረፍህ ቁስል እኔ የተፈወስኩት
በመስቀል በመሞትህ ከሞት አመለጥኩኝ ፤
አዝማች · Chorus
ኤሎሄ ላማሰበቅታኒ እስክትል የተሰቃየኸው
ስለእኔ ሞትህ ልታድነኝ በበዛው የመስቀል ጣርህ
ስለእኔ ለከፈልከው ዋጋ
መታሰቢያ ላድርግ እስኪ ዛሬ
ለመክፈል ዋጋ ካሣ ባይኖረኝም
ቁጥር 4 · Verse 4
ላክብርህ በፊትህ ዘምሬ (፪)
ቁጥር 5 · Verse 5
እስኪ የተደረገልንን እናስባለን!
የቀራንዮን ፍቅር እናስባለን!
በመከራ ሰዓት!
በመከራ ሰዓት በዚያ ጭንቀትህ
ዓብ አባትህ እንኳ ዝም አለ ተወህ
የሁላችን በቀል በላይህ ላይ ሆነ
በመስቀል እንዳንተ የለም የታመነ
አዝማች · Chorus
ኤሎሄ ላማሰበቅታኒ እስክትል የተሰቃየኸው
ስለእኔ ሞትህ ልታድነኝ በበዛው የመስቀል ጣርህ
ስለእኔ ለከፈልከው ዋጋ
መታሰቢያ ላድርግ እስኪ ዛሬ
ለመክፈል ዋጋ ካሣ ባይኖረኝም
ቁጥር 6 · Verse 6
ላክብርህ በፊትህ ዘምሬ (፪)
ቁጥር 7 · Verse 7
ሃሌሉያ! ስለእኛ የታረድክ!
ለዘላለም ተባረክ!
የእኛ ጌታ!
ልታዘዝህ ዛሬ ደስ ላሰኝህ
ክብርህን ላያት ጣርህን አስቤ
ዋጋ ከፍለህልኝ ሰው አድርገኸኛል
ክበር የእኔ ጌታ ደምህ ፈሶልኛል
አዝማች · Chorus
ኤሎሄ ላማሰበቅታኒ እስክትል የተሰቃየኸው
ስለእኔ ሞትህ ልታድነኝ በበዛው የመስቀል ጣርህ
ስለእኔ ለከፈልከው ዋጋ
መታሰቢያ ላድርግ እስኪ ዛሬ
ለመክፈል ዋጋ ካሣ ባይኖረኝም
ቁጥር 8 · Verse 8
ላክብርህ በፊትህ ዘምሬ (፪x)
ቁጥር 9 · Verse 9
ሃሌሉያ!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ