በኔ ላይ ልትሰራ
Benie Lay Letsera
2010 · ትራክ 1 · 6:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በእኔ ላይ ልትሰራ ጌታ የወደድከዉ
ምኔ ደስ ቢልህ እንዴት ብትወደኝ ነው (፪x)
ምንም ሳልሰራ ወደድከኝና
ጌታ በደምህ ገዛኸኝና
ከመሬት ከአፈር አነሳኸኝ
ሰው ያላየዉን አሳየኸኝ
አይገርምም ወይ ኧረ አይገርምም ወይ
አይደንቅም ወይ ኧረ አይደንቅም ወይ
ቁጥር 2 · Verse 2
በእኔ በትንሹ ሲሰራ መንፈሱ አሄ
ተራዉ ሰዉ/ውዳቂው ከመሬት ተነስቶ
ሲያመልክህ እጆቹን አንስቶን
መንፈስህ መጥቷል በጉባኤዉ
የነካዉ ያመስግነዉ ዛሬ (፪x)
አዝማች · Chorus
አይገርምም ወይ ኧረ አይገርምም ወይ
አይደንቅም ወይ ኧረ አይደንቅም ወይ
በእኔ በትንሹ ሲሰራ መንፈሱ አሄ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከኃጢአቴ በቀር አላዉቅም
አንድም ሚያስመሰግነኝ የለም
ጌታ ግን እጆቹን ዘርግቶ
ሰራብኝ አንደበቴን ከፍቶ (፪x)
አዝማች · Chorus
አይገርምም ወይ ኧረ አይገርምም ወይ
አይደንቅም ወይ ኧረ አይደንቅም ወይ
በእኔ በትንሹ ሲሰራ መንፈሱ አሄ
ቁጥር 4 · Verse 4
የሚሆነዉ ነገር ገርሞኛል
ጉባኤዉ በክብርህ ተሞልቷል
ዝም ብዬ ክብርህን ሳየዉ
ኦ እኔ ማን ነኝ በዬ እላለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በእኔ ላይ ልትሰራ ጌታ የወደድከዉ
ምኔ ደስ ቢልህ እንዴት ብትወደኝ ነው (፪x)
ምንም ሳልሰራ ወደድከኝና
ጌታ በደምህ ገዛኸኝና
ከመሬት ከአፈር አነሳኸኝ
ሰው ያላየዉን አሳየኸኝ
አዝማች · Chorus
አይገርምም ወይ ኧረ አይገርምም ወይ
አይደንቅም ወይ ኧረ አይደንቅም ወይ
በእኔ በትንሹ ሲሰራ መንፈሱ አሄ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ