Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሕይወት ይናገር

Hiwot Yenager

2010 · ትራክ 2 · 7:55 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሕይወት ይናገር እስቲ (፬x)

ወሬ አይደለም ምላሳችን

ይናገራል ሕይወታችን

ሕይወታችን

መመስከር መጸለይ ነበር ሕይወትህ

መንፈሳዊ ዓለም ላይ ከብዶ ቃላትህ

ዛሬ ግን የታለ የድሮ ፍቅርህ

ሁሉም ተቀየረ አረማመድህ የታለ ሕይወትህ

ሕይወት ይናገር እስቲ (፬x)

ወሬ አይደለም ምላሳችን

ይናገራል ሕይወታችን

ሕይወታችን

ያልኖርንበትን ተናጋሪ ተናጋሪ

ውስጣችን ሲታይ አሳፋሪ አሳፋሪ

ለታይታ መኖር ቀርቶብን

ጌታን ያክብረው ጓዳችን

የአደባባይ ላይ ፉከራ

ቤታችን ይታይ ሲሰራ

ጽድቅን ስትከተል በረከትህ ይመጣል

መንግሥቱን ስትሻው ሌላው ይጨመራል

ገንዘብን ግን መውደድ የኃጢአት ስር ነው

ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችልም ቃሉ እንደሚለው

ሕይወት ይናገር እስቲ (፬x)

ወሬ አይደለም ምላሳችን

ይናገራል ሕይወታችን

ሕይወታችን

ሆዳቸው ሆኖ አምላካቸው አምላካቸው

ባሪያ አድርጐ ሲገዛቸው ሲገዛቸው

ቅባቱን ጥሎ ነጐደ የሥጋን ነገር ወደደ

ለትውልድ የሚበቃ ሰው ወርቅና ገንዘብ ሲያታልለው

ሕይወት ይናገር እስቲ (፬x)

ወሬ አይደለም ምላሳችን

ይናገራል ሕይወታችን

ሕይወታችን

ክርስቲያን ነኝ ካሉ መኖር እንደቃሉ

አገልጋይ ነኝ ካሉ መኖር እንደቃሉ

ክርስትና ማለት መስቀል መሸከም ነው

እግዚአብሔርን መስሎ በሕይወት መኖር ነው ፤ ቃሉን መተግበር ነው

ሕይወት ይናገር እስቲ (፬x)

ወሬ አይደለም ምላሳችን

ይናገራል ሕይወታችን

ሕይወታችን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ