በርታና ጽና
Bertana Tsina
2015 · ትራክ 2 · 4:40 · አማርኛ · የተስፋ
ቁጥር 1 · Verse 1
መንገዱ ቢጠብብ አትፍራ
ጉዞው ቢረዝም አትድከም
ከፊትህ የሚሄድ አለና
የሚያዘጋጅ መንገድህን
አዝማች · Chorus
በርታና ጽና ይላል ጌታ
አትፍራ አትደንግጥ
በምትሄድበት ሁሉ
ከአንተ ጋር ነኝ ይላል
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢያሱን ያበረታ አምላክ
ዛሬም ይናገራል
ዮርዳኖስ ይከፈላል
ኢያሪኮ ይፈርሳል
አዝማች · Chorus
በርታና ጽና ይላል ጌታ
አትፍራ አትደንግጥ
በምትሄድበት ሁሉ
ከአንተ ጋር ነኝ ይላል
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ