Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እፈልግሃለሁ

Efelegehalehu

ትራክ 1 · 8:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እጄን ከፍ አድርጌ ለአንተ አነሳለሁ

ርሃቤም ጥማቴም ናፍቆቴም አንተን ነው

በሕይወቴ አክብረው እየሱስን አድምቀው

ጌታ መንፈስ ቅዱስ እፈለግሃለሁ

እፈልግሃለሁ (8x)

ሕይወቴም ኑሮዬም ይሁን ያለህበት

አንተ የምትመራው ሁሌ የምታዝበት

መኖር አልፈልግም እንዲሁ በመላ

በዘመኔ አይግዛኝ ማንም ከአንተ ሌላ

እፈልግሃለሁ (8x)

ፍቅርህን በልቤ በውስጤ አፈሰስከው

ወደ እውነት ልትመራኝ ከላይ የተላከው

ስህተት የማያውቅሀ አስተማሪዬ ነህ

ከምንም ከማንም ትበልጥብኛለህ

እፈልግሃለሁ (8x)

ያለ አንተ መገኘት ሕይወት ጣዕም የለውም

ብበላም ብጠጣም ከቶ አያጠግበኝም

ልቤን የምትሞላው በሃሴት በደስታ

እፈልግሃለሁ ጥዋት ሳልል ማታ

ያለ አንተ መገኘት ሕይወት ጣዕም የለውም

ሁሉን እንኳን ባገኝ ከቶ አያረካኝም

ውስጤን የምትሞላው በክብርህ በደስታህ

እፈልግሃለሁ ጥዋት ሳልል ማታ

እጄን ከፍ አድርጌ ለአንተ አነሳለሁ

ርሃቤም ጥማቴም ናፍቆቴም አንተን ነው

በሕይወቴ አክብረው እየሱስን አድምቀው

ጌታ መንፈስ ቅዱስ እፈለግሃለሁ

እፈልግሃለሁ (8x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ