Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንካ ዘላለሜን

Enka Zelalemien

2014 · ትራክ 1 · 6:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በራሴማ ብዙ ዘመን ለፍቻለሁ

በራሴማ ብዙ ዘመን እሮጫለሁ (፪x)

ያላንተማ ደስ ብሎት ተድላን የቀመሰ እንደሌለ

በጐ ስጦታ ፍፁም በረከት ከላይ እንደሆነ (፪x)

የገባኝ ያው ብዙ ለፍቻለሁ

ዛሬ ግን በቃ አቅም አጥቻለሁ

ያስጨነቀኝ የረበሸኝ የዛሬውን ነገሬ

ብቻ አይደለም ሰጠሁህ ጌታ ለአንተ ዘመኔን

እንካ ዘላለሜን እንካ (እንካ)

እንካ ዘላለሜን እንካ (፪x)

እንካ ሰጥቻለሁ ዘል-ዘለዓለሜን (ዘላለሜን)

ለአንተ ሰጥቻለሁ ይኸው ኑሮዬን

በቃ ሰጥቻለሁ ዘል-ዘለዓለሜን (በቃ)

ጌታ ሰጥቻለሁ ይኸው ዘመኔን

በራሴማ ብዙ ዘመን ለፍቻለሁ

በራሴማ ብዙ ዘመን እሮጫለሁ (፪x)

በከንቱ ይደክማል ቤተ ሰሪ

በከንቱ ቅጥር ጠባቂ

በሌለህበት ከንቱ ሩጫ

መውደቅ መላላጥ መታመም ብቻ (፪x)

የገባኝ ያው ብዙ ለፍቻለሁ

ዛሬ ግን በቃ አቅም አጥቻለሁ

ያስጨነቀኝ የረበሸኝ የዛሬውን ነገሬ

ብቻ አይደለም ሰጠሁህ ጌታ ለአንተ ዘመኔን

እንካ ዘላለሜን እንካ (፬x)

እንካ ሰጥቻለሁ ይኸው ዘለዓለሜን

ለአንተ ሰጥቻለሁ ይኸው ዘመኔን

በቃ ሰጥቻለሁ እንካ ዘላለሜን (በቃ)

ጌታ ሰጥቻለሁ ውሰድ ዘመኔን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ