ጆሮዬን ልብሳ
Joreyen Libesa
ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃጥያት አላገኘህም
ስንፍና አልከሰሰህም
ስትገዛ አልደከመህም
እርጅና አላወቀህም(፪)
አዝማች · Chorus
እኔም አላውቅህም የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም(፪)
እኔም አላውቅህም የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም(፪)
የለህም እኩያ
የለህም አምሳያ
ትልቅ ነህ ሃሌሉያ(፪)
ትልቅ ነህ ሃሌሉያ(፬)
ቁጥር 2 · Verse 2
የነገሥታት ወገብ ትጥቅ የምታስፈታ
ሓያል አምላክ የጌቶች ጌታ(፫)
የፍጥረት መገኛ ሕያው መሠረት
አትሰላ በዓመታት አትደመር በዘመናት
አትሰላ በዓመታት
የትኛውም ምሑር ሒሳብ አይሰራህም
የትኛውም ሰዓሊ ብሩሽ አይቀባህም
የቱም አንጠረኛ ቀርጾ አያወጣህም
አሐዱ አትባልም ደረጃም የለህም
አዝማች · Chorus
ኧረ እኔስ ለክብርህ ኧረ እኔስ ለዝናህ
ሽርጉድ ልበል ላገልግልህ
ጆሮዬን ልብሳ ልኑልርህ(፪)
ልኑርልህ(፬)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስቲ የማን ጀግና ሞትን አሸነፈ
እስቲ የማን ጀግና ጨለማ ገፈፈ
እስቲ የማን ጀግና ሲዖልን ድል ነሳ
ኢየሱስ ብቻ ነህ የይሁዳ አንበሳ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ኢየሱስ ብቻ ነህ
ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ዙፋንህ የጸና
ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ኢየሱስ ብቻ ነህ
ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ዙፋኑ የጸና
ዙፋንህ የጸና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ