ቅዱስ ቅዱስ
Kidus Kidus
2022 · ትራክ 2 · 6:28 · አማርኛ · አምልኮ
ቁጥር 1 · Verse 1
በፊትህ ስቆም በመገረም
ክብርህን ሳይ በትሕትና
ከሱራፌል ጋር እጮሃለሁ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያልኩ
አዝማች · Chorus
ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ
ምድር ሁሉ በክብርህ ተሞላች
ቅዱስ ቅዱስ አንተ ብቻ
የሚመስልህ ማንም የለም
ቁጥር 2 · Verse 2
ዙፋንህ ጸንቷል ለዘላለም
መንግሥትህ አያልፍም ድንበር የለውም
ትውልድ ለትውልድ ይሰግድልሃል
ያልተፈጠረ ገና ያመሰግንሃል
አዝማች · Chorus
ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ
ምድር ሁሉ በክብርህ ተሞላች
ቅዱስ ቅዱስ አንተ ብቻ
የሚመስልህ ማንም የለም
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ