Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተን ሳላይ

Anten Salay

2022 · ትራክ 3 · 5:52 · አማርኛ · አምልኮ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተን ሳላይ ቀኔ አይሞላም

ድምጽህን ሳልሰማ ልቤ አያርፍም

እንደ ዋላ ውሃ እንደምትናፍቅ

ነፍሴ አንተን ትጠማለች

ፊትህን አሳየኝ በማለዳ

ቃልህን አሰማኝ በሌሊት

ከአንተ ጋር መሆን ይበልጣል

ከሺህ ቀን በሌላ ስፍራ

ያማረ ነገር በምድር ቢኖር

ካንተ ውጭ ምን አለኝ በሰማይ

ሥጋዬ ቢያልቅ ልቤ ቢደክም

አንተ የልቤ ጽናት ነህ

ፊትህን አሳየኝ በማለዳ

ቃልህን አሰማኝ በሌሊት

ከአንተ ጋር መሆን ይበልጣል

ከሺህ ቀን በሌላ ስፍራ

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ