ለእኔ ነበር
Lenie Neber
2014 · ትራክ 1 · 4:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔ ነበር ያኔ መንገላታትህ
በግርፍና በጦር መቁሰልህ
መስቀል ተሸክመህ መውጣትህ
ሚስማር ተቸንክሮብህ መሞትህ
ለእኔ ነበር ያ ሁሉ መንገላታትህ
በሰዎች ፊት ተዋርደህም መሞትህ
አዝማች · Chorus
ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምን አይነት ክብር ምን አይነት ፍቅር ነው
ያለህ ከኤደን ምድር ለወጣነው
አመጣጥ አሰራርህ ልዩ ነው
ላመስግንህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
ምን አይነት ክብር ምን አይነቱ ፍቅር ነው
ለእኔ በኃጢአት . (1) .
አዝማች · Chorus
ሃሌሉ ሃሌሉያ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሰማዩ ከክብር ዙፋንህ
ልታስታርቀን ከእግዚአብሔር ከአባትህ
ከማንም በላይ ገነህ ለከበርከው
ከዚያ ወርደህ ለእኛ ቤዛ የሆንከው
ግን አልቀረህም አልከለከለህ መቃብር
ተነሳህ ድል አድርገህ ለሞት ሳትበገር (ሳትበገር)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉ ሃሌሉያ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ