Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ልዩ ነህ

Leyu Neh

2017 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በፈለግኩሀ ቁጥር አገኝሃለሁ

ባገኘሁህ ቁጥር ይበልጥ እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ኢየሱስ እወድሃለሁ(፪)

ልዩ ልዩ ነህ አምላኬ(፪)

እንዳንተ አጣሁኝ ፈልጌ(፬)

ብዙ ይቅር ያልከው ብዙ ይወድሃል

ጥቂት የተውክለት እንደዛው ይኖራል

እግርህን በእንባዬ እያረሰረስኩ

ሽቶዬን ልቀባ . (1) .

አባቴ ለእኔ ያረግኸው ብዙ ነው

የምሥጋና አልባስጥሮሴን ልስበረው

ይኸውና ማደርያህን ያውደው

አምልኮዬ ዙፋንህን ያጥለቅልቀው

አባቴ ለእኔ ያረግኸው ብዙ ነው

የምሥጋና አልባስጥሮሴን ልስበረው

ይኸውና ማደርያህን ያውደው

ለውለታህ መታሰብያው ይሄ ነው

እንደ ሰው አይደለህም እንደ ራስህ እንጂ

ወደ አንተ የመጡትን አታወጣም ከደጅ

አትለዋወጥም አንተ የእኔ ወዳጅ

ወረትን አታውቅም አንተ የእኔ ወዳጅ

እኔማ ተባረክ ልበል እንጂ

ሲታወቀኝ እንደያዘኝ መልካም እጅህ

የእኔ ጌታ ለእኔ ያረግኸው ብዙ ነው

የምሥጋና አልባስጥሮሴን ልስበረው

ልጄ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ብለህ

ኪዳንህን አጸናህ በራስህ ተማምለህ

ሰማዩን ዝቅ አርገህ አየሁህ ስትመጣ

እኔን መጥተህ ማየት ባለህበት ቦታ

አባቴ ለእኔ ያረግኸው ብዙ ነው

የምሥጋና አልባስጥሮሴን ልስበረው

ይኸውና ማደርያህን ያውደው

አምልኮዬ ዙፋንህን ያጥለቅልቀው

አባቴ ለእኔ ያረግኸው ብዙ ነው

የምሥጋና አልባስጥሮሴን ልስበረው

ይኸውና ማደርያህን ያውደው

ለውለታህ መታሰብያው ይሄ ነው

በፈለግኩሀ ቁጥር አገኝሃለሁ

ባገኘሁህ ቁጥር ይበልጥ እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ኢየሱስ እወድሃለሁ(፪)

ልዩ ልዩ ነህ አምላኬ(፪)

እንዳንተ አጣሁኝ ፈልጌ(፬)

እወድሃለሁ እወድሃለሁ(፫)

ኢየሱስ እወድሃለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ