Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ልዘምርለት

Lezemerelet

ትራክ 1 · 5:22 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጠብቆኝ እኮ ነው ዛሬ ያለሁት ከጠላቴ ዛቻ

መቼ እወጣው ነበር ለብቻዬ ያንን ሁሉ ጣጣ

በጐኔ ሳይርቀኝ ሳይለየኝ ከክፉ ጠብቆ

መንገዴን አንቅቶ ጀምሬያለሁ የሰላምን ጉዞ

በክፉ ቀን ያልተለየኝ

በሃዘኔ ከቶ ያልሸሸኝ

እውነተኛ ወዳጅ አለኝ

እውነተኛ ወዳጅ አለኝ

በክፉ ቀን ያልተለየኝ (፪x)

ብዘምርለት መች ይበቃዋል ብዘምርለት (፬x)

ካረገው ጋራ መች ሊወዳደር የእኔ መዘመር

በእስራኤል/በኤፍሬም ላይ ሟርትም አይሰራ

ድንጋጤም ቤቱ አይገባ

እግዚአብሔር ቅጥር ሆኖታል

በከፍታ ያዘምረዋል (፬x)

እንደ ትላንትናው መስሎ ጠላት ሊያጠፋኝ ሲመጣ

ዛሬ ግን ቤቴ አለ ኢየሱሴ የሰላም አለቃ

ደሙ በመቃኔ በጉበእኔ ላይ ስለተቀባ

አልቻለም ጠላቴ እንደድሮ ወደ እኔ ሊጠጋ

በክፉ ቀን ያልተለየኝ

በሃዘኔ ከቶ ያልሸሸኝ

እውነተኛ ወዳጅ አለኝ

እውነተኛ ወዳጅ አለኝ

በክፉ ቀን ያልተለየኝ (፪x)

በእስራኤል/በኤፍሬም ላይ ሟርትም አይሰራ

ድንጋጤም ቤቱ አይገባ

እግዚአብሔር ቅጥር ሆኖታል

በከፍታ ያዘምረዋል (፬x)

ትጠፋለህ ብሎ የደገመው ጠላቴ የታለ

ኧረ እኔስ አለሁኝ በሕይወቴ ኢየሱስ ስለለ

በአንዳች አልጨነቅ አልሸበር ለነገም አልፈራ

በአንድ የመጣው ጠላት ይበተናል በሰባት ጐዳና

በክፉ ቀን ያልተለየኝ

በሃዘኔ ከቶ ያልሸሸኝ

እውነተኛ ወዳጅ አለኝ

እውነተኛ ወዳጅ አለኝ

በክፉ ቀን ያልተለየኝ (፪x)

ብዘምርለት መች ይበቃዋል ብዘምርለት (፫x)

ካረገው ጋራ መች ሊወዳደር የእኔ መዘመር

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ