ምን እሻለሁ
Men Eshalehu
ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ
አምላኬ አምላኬ አምላኬ
ምን እሻለሁ ባይኖችህ ታይቻለሁ
ምን እሻለሁ በጆሮህ ተሰምቻለሁ
ምን እሻለሁ በእጆችህ ተይዣለሁ
ምን እሻለሁ በፊትህ ከብሬአለሁ
የእግዚአብሔር መንፈስ ደስ የሚያሰኝ ደስ የሚያሰኝ
ደስ የሚል መንፈስ ደስ የሚያሰኝ ደስ የሚያሰኝ
የሚያረሰርስ ደስ የሚያሰኝ ደስ የሚያሰኝ
ደስታን ይሞላል ይባርካል
ሕዝቡን በእጆቹ ይዳስሳል
የተራበች ነፍስ ትጠግባለች
ያዘነችውም ትጽናናለች
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር መንፈስ ...
ቁጥር 2 · Verse 2
ተራራው ሜዳ የሆነው
በመንፈስ እንጂ መች በብርታት ነው
ቁርጭምጭሚትን የምታጸና
የሕዝብህ ጉልበት አንተ ነህና
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር መንፈስ ...
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰላምህ ፈሰሰ እንደ ጅረት
አርነት በዛ ባለህበት
ደንዳናው ሁሉ ፈራረሰ
በመንፈስህ ዘይት ረሰረሰ
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር መንፈስ ...
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ