Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምሥጋና ምሥጋና

Mesgana Mesgana

1993 · ትራክ 10 · 4:17 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ

በዕልልታ በዕልልታ በሽብሸባ በሽብሸባ

ይዤ ወደ መቅደሱ ልግባ

ይዤ ወደ ማደሪያው ልግባ

እጅግ (፫x) የከበረ

ሥሙም ያለ የሚኖር የነበረ

እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ነውና

ልግባ ላምላኬ ልሰጥ ምሥጋና

ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ

በዕልልታ በዕልልታ በሽብሸባ በሽብሸባ

ይዤ ወደ መቅደሱ ልግባ

ይዤ ወደ ማደሪያው ልግባ

ምርኮኛ የነበርኩ ለጠላት

ባለ እግርና ባለ እጅ ሰንሰለት

ዛሬ ግን የታል ተበጣጥሷል

የሞት ድምጽ ከእኔ ተወግዷል

ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ

በዕልልታ በዕልልታ በሽብሸባ በሽብሸባ

ይዤ ወደ መቅደሱ ልግባ

ይዤ ወደ ማደሪያው ልግባ

እጅግ ወደ አማረ ማደሪያው

ብዙ በረከት ወደ ሚያፈሰው

እንድገባ ወዶኛልና

ልስገድ ልቀኝ በደስታ ዜማ

ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ

በዕልልታ በዕልልታ በሽብሸባ በሽብሸባ

ይዤ ወደ መቅደሱ ልግባ

ይዤ ወደ ማደሪያው ልግባ

ውርደቴን በክብር ለውጧል

ሸክሜን ከላዬ ላይ አንስቷል

ለምን እሆናለሁ እንዳልተፈታ

እስኪ ላዚምለት በእልልታ

ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ

በዕልልታ በዕልልታ በሽብሸባ በሽብሸባ

ይዤ ወደ መቅደሱ ልግባ

ይዤ ወደ ማደሪያው ልግባ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ