ምስኪን ወደአንተ ሲጠጋ
Meskin Wedante Sitega
ትራክ 7 · 3:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትዕቢት የተሞላው ጐልያድ ወደቀ
በአንተ የታመነውን ዳዊትን የናቀ
አንተን ይዞ ወጥቶ ታናሽ ብላቴና
ግዙፉን ዘረረው ስምህን ጠራና
አዝማች · Chorus
ምስክኪን ወደ አንተ ሲጠጋ ጋሻ መከታ ፍለጋ
ገፍተኸው መቼ ታውቃለህ በእቅፍህ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ድንኳንህ ያድራል በቤትህ የለመልማል
ሰላሙን ታበዛዋለህ ጠላቱን ትመታዋለህ
ጠላቱን ትመታዋለህ!
ቁጥር 2 · Verse 2
የሚጤሰውን ጧፍ ከቶ አታጠፋም
የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አትሰብርም
ድካሙን ተረድቶ አንተን የተጠጋ
በቅዱሱ ስፍራ ከበረ ከአንተ ጋር
አዝማች · Chorus
ምስክኪን ወደ አንተ ሲጠጋ ጋሻ መከታ ፍለጋ
ገፍተኸው መቼ ታውቃለህ በእቅፍህ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ድንኳንህ ያድራል በቤትህ የለመልማል
ሰላሙን ታበዛዋለህ ጠላቱን ትመታዋለህ
ጠላቱን ትመታዋለህ!
ቁጥር 3 · Verse 3
መሰማሪያ አጥቶ የባዘነ ሕይወት
መቅበዝበዙ ቀረ ሲገባ በአንተ ቤት
እንደለመለመ የወይራ ዛፍ ሆኗል
ምስኪኑ በአንተ ይኸው ከፍ ብሏል
አዝማች · Chorus
ምስክኪን ወደ አንተ ሲጠጋ ጋሻ መከታ ፍለጋ
ገፍተኸው መቼ ታውቃለህ በእቅፍህ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ድንኳንህ ያድራል በቤትህ የለመልማል
ሰላሙን ታበዛዋለህ ጠላቱን ትመታዋለህ
ጠላቱን ትመታዋለህ!
ቁጥር 4 · Verse 4
ስምህ እግዚአብሔር ሆይ የጸና ግንብ ነው
ለደካማው ብርታት ለምስኪን መጠጊያው
ያስጨናቂን ቀንበር ጸባብራለህ
በሰማይ በምድር በቅን ትፈርዳለህ
አዝማች · Chorus
ምስክኪን ወደ አንተ ሲጠጋ ጋሻ መከታ ፍለጋ
ገፍተኸው መቼ ታውቃለህ በእቅፍህ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ድንኳንህ ያድራል በቤትህ የለመልማል
ሰላሙን ታበዛዋለህ ጠላቱን ትመታዋለህ
ጠላቱን ትመታዋለህ!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ