Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዋጋ ያስከፍላልና

Waga Yaskefelalena

ትራክ 9 · 6:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዋጋ ያስከፍላልና ክርስትና ገና ምኑ ተያዘና

የአባቶቼን ወግ አይቼ የነቢያትና የሐዋርያትን ፅዋ ጠጥቼ

ሽልማቴን እቀበላለሁ

ገና ዋጋ እከፍላለሁ

የቀድሞ ነቢያትና ሐዋርያት ደምና እንባ

ታስቦ በፊትህ ዋጋ አግኝቷልና አባባ

ዛሬም በእምነት ቆሜ እጠብቃለሁ

ዋጋ ከፍዬበት አክሊሌን እወስዳለሁ

ዋጋ ያስከፍላል ከየሱስ ጋር ኑሮ

በዓለም ተሰዶ ተጎሳቁሎና ተባሮ

የህይወትን አክሊል ለመቀበል

ላለፉት ለእኔም ዋጋ ያስከፍላል

የፅድቅና የድል አክሊል በላይ ተዘጋጅቶ

ከጌታ ልቀበል በወንጌል እምነቴም ጸንቶ

በእግር ግንድ እስራት ተጨንቄ

ብድራቴን ከእጁ ወስዳለሁ ጠብቄ

በድንጋይ ውግራት በመጋዝም ተሰንጥቄ

በዘይት ቅቅላት በአንበሳ አፍ ተነጥቄ

ሽልማቴም የክብር አክሊል ነው

ከአምላክ እጅ ልቀበል ጊዜያቱ ቅርብ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ