Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ታማኝ ነው

Tamagn New

2005 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል

ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል

በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ

ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ

ወላጅ አልባን አሳዳጊ የተጣለውን ፈላጊ

ስለጠላቱ የሞተ ብቻውን ድንቅን አድራጊ

የጠፋውን ሰው መልሷል የስንቱን ሸክም አራግፏል

በምድረበዳ ተገኝቶ ከአለት ውስጥ ምንጭን ያፈልቃል

ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል

ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል

በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ

ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ

ፍቅሩ ከሞት ውስጥ ያወጣል በቅንነቱ ይመራል

ለተጠማ ከህይወት ውኃ በነጻ እንዲሁ ይሰጣል

ለቸርነቱ ልክ የለው አይቋረጥ ልግስናው

አንድ ቀን ጎድሎበት አያውቅ አምላኬ ሁሌ ሙሉ ነው

ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል

ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል

በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ

ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ

ታማኝነቱ ብዙ ነው ቃልኪዳኑንም ያከብራል

እንደተነገረ የሚያደርግ እንደ እግዚአብሔር የት ይገኛል

በማንም አይገመትም ሳይነግሩት የልብን ያውቃል

የእስረኛውን ወጥመድ ሰብሮ በከፍታ ላይ ያኖራል

ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል

ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል

በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ

ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ

ፍቅሩ ከሞት ውስጥ ያወጣል በቅንነቱ ይመራል

ለተጠማ ከህይወት ውኃ በነጻ እንዲሁ ይሰጣል

ለቸርነቱ ልክ የለው አይቋረጥ ልግስናው

አንድ ቀን ጎድሎበት አያውቅ አምላኬ ሁሌ ሙሉ ነው

ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል

ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል

በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ

ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ