Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ትንሳዔውን ተናገሩ

Tensaewen Tenageru

2009 · ትራክ 1 · 4:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አበቃለት ተብሎ ነበር ኢየሱሴ ሲቀበር

ወሬ ሆኖ ሊቀር

አለፈ ተብሎ ቢወራ ነበር ተብሎ ሊዘከር

ወሬ ሆኖ ሊቀር

የዓለምን ታሪክ ለወጠ ነገር ተገለበጠ

የአዳም ዘር አመለጠ

መቃብሩን ፈነቃቅሎ ሰይጣንን ጉድ አረገ

ወደ አባቱ አረገ

የሰው ኃጢአት ተወገደ ተሻረ የእኛ አበሳ

በትንሳዔው ድል ነሳ

መቼ እንደሞተ ቀረ ከሙታንም ተነሳ

በትንሳዔው ድል ነሳ

ኢየሱስ ተነሳ

ጌታዬ ተነሳ (፪x)

ትንሳዔውን ተናገሩ የእምነት አባቶች መሰከሩ

እኔም ለትውልድ ልናገርው

ኢየሱስ ተነስቷል ልመስክረው (፪x)

ተነስቷል ይሄ ጌታ

ማኅተሙን እርሱ ፈታ

ቅዱሳን በአንድ ሁኑና

አክብሩት ከእኔ ጋራ (፪x)

ዕልልታ ሙገሳ ሞትን ድል ለነሳ

ኢየሱስ ድል ነስቷል አክብሩት ቅዱሳን

የታል ዕልልታ ለአዳነን ጌታ

የታል ጭብጨባ መቅደስ የሚገባ (፪x)

ኃይል እንደሌለው ቢመታ ወደ መስቀል ቢነዳ

በትንሳዔው ድል ነሳ

በእንጨት ላይ ቢንጠለጠል ስለ ሰው ልጅ ቢጐዳ

በትንሳዔው ድል ነሳ

ቢያሾፉ ቢያሳልቁበት እያሉ በል ውረዳ

በትንሳዔው ድል ነሳ

በደሙ እርቅ አወረደ አፈረሰ ያን ግድግዳ

በትንሳዔው ድል ነሳ

ኢየሱስ ተነሳ ጌታየ ተነሳ(፪×)

ትንሳዔውን ተናገሩ የእምነት አባቶች መሰከሩ

እኔም ለትውልድ ልናገርው

ኢየሱስ ተነስቷል ልመስክረው (፪x)

ተነስቷል ይሄ ጌታ

ማኅተሙን እርሱ ፈታ

ቅዱሳን በአንድ ሁኑና

አክብሩት ከእኔ ጋራ (፪x)

ዕልልታ ሙገሳ ሞትን ድል ለነሳ

ኢየሱስ ድል ነስቷል አክብሩት ቅዱሳን

የታል ዕልልታ ለአዳነን ጌታ

የታል ጭብጨባ መቅደሱ የሚገባ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ