ያችን ቀን
Yachin Ken
6:00 · አማርኛ · የተስፋ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያችን ቀን ሳስባት ልቤ ይዘላል
ፊትህን የማይበት ያች ዕለት
እንባ የሌለባት ሞት የማይደርስባት
የዘላለም ጧት ስትነጋ
አዝማች · Chorus
እመጣለሁ ብለሃል ትመጣለህ
ቃልህ እውነት ነውና
በደመና ላይ በክብር ስትገለጥ
ዓይኔ ያንተን ፊት ያያል
ቁጥር 2 · Verse 2
እስከዚያች ቀን ድረስ እታገሳለሁ
ሥራህን እሠራለሁ
መብራቴን አብርቼ እጠብቃለሁ
ሙሽራው እስኪመጣ
አዝማች · Chorus
እመጣለሁ ብለሃል ትመጣለህ
ቃልህ እውነት ነውና
በደመና ላይ በክብር ስትገለጥ
ዓይኔ ያንተን ፊት ያያል
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ