ያንተ መልካምነት
Yante Melkamenet
2019 · ትራክ 13 · 6:29 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በጨለመው አለም ምንም በሌለበት/2
ልቤን ያሞቀዋል ያንተ መልካምነት
ያንተ መልካምነት ኦሆ
ቁጥር 1 · Verse 1
አላጉረመርምም እግዚአብሔር አምላክ ነው ይረዳኛል
ከሁኔታ በላ የሚያኖር እርሱ ነው እጄን ይዞኛል
ጨላማው ቢበረታ አምላክ አለኝ የማይረታ
አትፍራ ብሎ ነግሮኛል የኔ ጌታ
ጨላማው ቢበረታ አባት አለኝ የማይረታ
አትፍራ ብሎ ነግሮኛል የኔ ጌታ
አዝማች · Chorus
በጨለመው አለም ምንም በሌለበት/2
ልቤን ያሞቀዋል ያንተ መልካምነት
ያንተ መልካምነት ኦሆ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሚሳነው የለም ሰማዩን በቃሉ አንጣሎታል
ምድርን ይሁን ብሎ በተዓምራቱ ሁሉን ፈጥሯል
ሁሉም ይገዛለታል ድል ነሺ የኔ ጌታ
አልፈራም ለልጆቹ ነው መከታ
ሁሉም ይገዛለታል ተዋጊ የኔ ጌታ
አልፈራም ለልጆቹ ነው መከታ
አዝማች · Chorus
በጨለመው አለም ምንም በሌለበት/2
ልቤን ያሞቀዋል ያንተ መልካምነት
ያንተ መልካምነት ኦሆ
ቁጥር 3 · Verse 3
ባህሩም ይታዘዛል መዕበሉም ይታዘዛል
ነፋሱም ይታዘዛል ውጀቡም ይታዘዛል
ጌታዬ ፀጥ በል ሲለው
ተፈጥሮ ድምፁን ይሳማል
ለእየሱስ ይታዘዘዋል ለጌታዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ