Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የአንተን ፍለጋ

Yanten Felega

2009 · ትራክ 9 · 4:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተክሎ መሄድ የአንተን ፍለጋ

ምነኛ መልካም ነው ቢበዛልኝ ፀጋ

አስከብሬህ ልለፍ እንደ አባቶቼ

ዓለም እና ትርፏን ሁሉን ንቄ ትቼ (፪x)

ክርስትናን መኖር ዋጋ በመክፈል ነው

ግን የለብስኩት ሥጋ እጅግ ደካማ ነው

ከጐኔ በመቆም ካላበረታኸኝ

ታውቃለህ ጌታ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ (፪x)

ዘወትር በፀሎት በፊትህ ልደፋ

በውስጤ ያኖርከው እሳቱ እንዳይጠፋ

ገና ላገልግልህ በኃይል ተሞልቼ

ጉብዝናዬን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼ (፪x)

ክርስትናን መኖር ዋጋ በመክፈል ነው

ግን የለብስኩት ሥጋ እጅግ ደካማ ነው

ከጐኔ በመቆም ካላበረታኸኝ

ታውቃለህ ጌታ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ (፪x)

ባላደራነቴን ችላ እንዳልለው

የወንጌልን ዕንቁ ለራ እንዳልጥለው

ታማኝ አድርገህ ቆጥረህ በቤትህ የሾምከኝ

ከፈተናዎቼ ፀጋህ ያሾልከኝ/ያስመልጠኝ (፪x)

ሰርክ እናይሳነኝ መንጋህን በመገብ

በሸክላ ዕቃ ውስጥ የከበረ መዝገብ

ያስቀመጥክ አንተ ነህ እንደ ኃይልህ ብዛት

እስከ መጨረሻው ሕይወቴን አግዛት (፪x)

ክርስትናን መኖር ዋጋ በመክፈል ነው

ግን የለብስኩት ሥጋ እጅግ ደካማ ነው

ከጐኔ በመቆም ካላበረታኸኝ

ታውቃለህ ጌታ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ