እኔ እገረማለሁ
Enie Egeremalehu
2009 · ትራክ 7 · 6:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ሁልጊዜ አመልክሃለሁ
ደግሜ ደግሜ ባነሳህ እኔስ መች ጠግባለሁ
የነፍሴ ንጉሥ ነህ አንተ የሕይወቴ መሪ
የፍጥረታት ጌታ ለዘለዓለም ነዋሪ
አዝማች · Chorus
እኔ እገረማለሁ (፫x) ፊትህን እያየሁ
እኔስ እደነቃለሁ (፫x) ማዳኑን እያየሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃሌሉ ሃሌሉያ
ልዘምር ልዘምር ሥምህን ላክብር
ልዘምር ልዘምር ጌታዬን ላክብር
በገናን ልደርድር በፊትህ ሥምህን ልቀድስ
ጣቶቼን ዘመቻ ያስተማርካቸው አንተ ነህ ኢየሱስ
በክብር ላይ ክብር ይጨመርልህ
በሰማይ በምድር አንተን አጣ የሚመስልህ
አዝማች · Chorus
እኔ እገረማለሁ (፫x) ፊትህን እያየሁ
እኔስ እደነቃለሁ (፫x) ማዳኑን እያየሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሃሌሉ ሃሌሉ-ያ
ልዘምር ልዘምር ሥምህን ላክብር
ልዘምር ልዘምር ጌታዬን ላክብር
በነጋ በጠባ ከውስጤ ምሥጋና ይፈልቃል
ያረክልኝ ተነግሮ ተዘምሮ መች ያልቃል
አንተ ነህ እንጂ ለእኔ ክብሬ ሌላ ክብር የለኝ
ከኃጢአት አጥበህ ቀድሰህ ሥም ያወጣህልኝ
አዝማች · Chorus
እኔ እገረማለሁ (፫x) ፊትህን እያየሁ
እኔስ እደነቃለሁ (፫x) ማዳኑን እያየሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሃሌሉ ሃሌሉ-ያ
ልዘምር ልዘምር ሥምህን ላክብር
ልዘምር ልዘምር ጌታዬን ላክብር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ