የጌቴሴማኒ
Yegethsemane/Yegetesemani
አማርኛ
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ (እህህ) የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ (አሄ እህህ) የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ (አሄሄ) ድንጋይ ተለቅሞ
(ኦ) ምርጥ የተባለን ዘር ከእርሱ ዘንዳ ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም (አሄሄ) መራራ ማፍራቱ
ይሁን ክፉ ፍሬ (አሃሃህ) ለጌታው መስጠቱ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለረዥም ከፍታ በአንተ ልብ የታጩ
ከፈቃድህ ርቀው በአጭር የተቀጩ
እንዲያ ከመሆን አድነኝ ጌታ
ፈቃድህ ያግኘኝ ከጥፋት ፈንታ
የእኔ አይሁን ግዛኝ አባቴ
ያልያ ግን ውድቀት ነው
ከንቱ ልፋቴ አዎ(፪x)
ፈቃድህ እንደሆነች በሰማይ
እንዲሁ በምድር ትሁን ጌታዬ
ፈቃድህ እንደሆነች በሰማይ አምላኬ
እንዲሁ በምድር ትሁን ጌታዬ
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ (እህህ) የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ (አሄ እህህ) የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ (አሄሄ) ድንጋይ ተለቅሞ
(ኦ) ምርጥ የተባለን ዘር ከእርሱ ዘንዳ ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም (አሄሄ) መራራ ማፍራቱ
ይሁን ክፉ ፍሬ (አሃሃህ) ለጌታው መስጠቱ
ቁጥር 2 · Verse 2
በፍሬያማው በዚያ ኮረብታ ላይ
በምድር ሆኜ ዜጋ የሰማይ
ዘመኔ ሙሉ አንተ እንድትገዛኝ
ፈቃዴን እሰጥሃለሁ መሻቴ ይህ ነው
ከእግሮችህ ስር ልሁን ጌታዬ
እርሱ ነው ክብር ያ ነው ምርጫዬ
አዎ ያ ነው ምርጫዬ
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ (እህህ) የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ (አሄ እህህ) የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ (አሄሄ) ድንጋይ ተለቅሞ
(ኦ) ምርጥ የተባለን ዘር ከእርሱ ዘንዳ ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም (አሄሄ) መራራ ማፍራቱ
ይሁን ክፉ ፍሬ (አሃሃህ) ለጌታው መስጠቱ
ቁጥር 3 · Verse 3
የጌቴሴማኒ የዕምባ ተክል
የቀራንዮ የደሙ ፍሬ ብቅለት
ጣ እሜ እንዳይሆን ደርሶ መራራ
ለመብል ሲታይ ሲያጐመራ
አምላኬ እግዚአብሔር ፈቃድህ ይግዛኝ
አውቃለሁ የእኔ ከቶ እንዳይጠቅመኝ
አዎ ከቶ አይጠቅመኝ
የወይኑ ቦታ አሄ (እህህ) የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ (አሄ እህህ) የወይኑ ቦታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ