የጌቴሴማኒ
Yegietiesiemani
2010 · ትራክ 2 · 6:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ አሄሄ ድንጋይም ተለቅሞ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኦ ምርጥ የተባለን ዘር ከእርሱ ዘንዳ
ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም አሄሄ መራራ ማፍራቱ
ይህን ክፉ ፍሬ አሃሃም ለጌታው መስጠቱ
ለረጅም ከፍታ በአንተ ልብ የታጩ
ከፈቃድህ ርቀው በአጭር ተቀጩ
እንዲያ ከመሆን አድነኝ ጌታ
ፈቃድህ ያግኘኝ ከጥፋት ፈንታ
የእኔ አይሁን ግዣኝ አባቴ
ያልያ ግን ውድቀት ነው ከንቱ ልፋቴ
አዎ ከንቱ ልፋቴ
ፈቃድህ እንደሆነች በሰማይ አምላኬ
እንዲሁ በምድርም ትሁን ጌታዬ (፪x)
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ አሄሄ ድንጋይም ተለቅሞ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኦ ምርጥ የተባለ ዘር ከእርሱ ዘንዳ
ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም አሄሄ መራራ ማፍራቱ
ይህን ክፉ ፍሬ አሃሃም ለጌታው መስጠቱ
በፍሬያማው በዚያ ኮረብታ ላይ
በምድር ሆኜ ዜጋዬ የሰማይ
ዘመኔን ሙሉ አንተ እንድትገዛኝ
ፈቃዴን እሰጥሃለሁ መሻቴ ይህ ነው
ከእግሮቼ ስር ልሁን ጌታዬ
እርሱ ነው ክብር ያ ነው ምርጫዬ
አዎ ያ ነው ምርጫዬ
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ አሄሄ ድንጋይም ተለቅሞ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኦ ምርጥ የተባለ ዘር ከእርሱ ዘንዳ
ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም አሄሄ መራራ ማፍራቱ
ይህን ክፉ ፍሬ አሃሃም ለጌታው መስጠቱ
የጌቴሴማኒ የእምባ ተክልህ
የቀራንዮ የደምህ ፍሬ ብቅለትህ
ጣዕሜ እንዳይሆን ደርሶ መራራ
ለመብል ሲታይ ሲያጐመራ
አምላኬ እግዚአብሔር ፈቅድህ ይግዛኝ
አውቃለሁ የእኔ ከቶ እንዳይጠቅመኝ
አዎ ከቶ አይጠቅመኝ
አዝማች · Chorus
የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
አወይ የወይኑ ቦታ አሄ እህህም የወይኑ ቦታ
በአግባብ ተቆፍሮ አሄሄ ድንጋይም ተለቅሞ
ቁጥር 4 · Verse 4
ኦ ምርጥ የተባለ ዘር ከእርሱ ዘንዳ
ከእርሱ ዘንታ ተክሎ
ኧረ እኔስ አልገባኝም አሄሄ መራራ ማፍራቱ
ይህን ክፉ ፍሬ አሃሃም ለጌታው መስጠቱ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ