ይህ ልቤን ተው በለው
Yeh Lebien Tew Belew
2013 · ትራክ 2 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኧረ ለምን ይሆን እንደዚህ
የራሴ እያለኝ የሰው የሚያስመኘኝ
ያለኝን አስቶ ሌላ የሚያሳየኝ
አዝማች · Chorus
ይህ ልቤን ተው በለው (፫x)
ይህ ልቤን ተው በለው (፪x)
ምከረው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳለኝ ብዙ ምክኒያት ተመስገን ምልበት
ምነው ማጉረሜ ሰነፍ ይሆንኩበት
ያለኝ ይበቃኛል ብዬ እያመሰገንኩ
አንተ በሰጠኸኝ አንተን እያከበርኩ
ልኑር እባክህ እርዳኝ የሌላ ሳልመኝ
ከበቂ በላይ ነው አንተ የሰጠኸኝ
ወገኔ መልካም ሲሆንለት
ምነው ልቤን ከፋው ደስታው ቅር አሰኘኝ
በመከራው እኑም ማመስገን ተሳነኝ
አዝማች · Chorus
ይህ ልቤን ተው በለው (፫x)
ይህ ልቤን ተው በለው (፪x)
ምከረው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ደስ ካለው ጋራ አብሮ ደስ ይበለኝ
ላዘነውም ደግሞ መጽናናት አድርገኝ
በጐ ህሊና ስጠኝ ሃሳቤንም አቅና
የአንተን ልብ አርግልኝ የእኔን ለውጥና
ፍቅርን ተላብሼ ትህትናን ደርቤ
ኖሬ ላስደስትህ በለኝ እንደ ልቤ
ያም ለእኔም ለእኔ ምኞቴ
እኔና ለእኔ ነው ሁልጊዜ ፀሎቴ
ጌታ ሆይ ለይልኝ እኔን ከእኔነቴ
አዝማች · Chorus
ይህ ልቤን ተው በለው (፫x)
ይህ ልቤን ተው በለው (፪x)
ምከረው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንዱ ሰቀናጣ ኖሮት ብዙ ነገር
ሀብቱ ተትረፍርፎ ለምርጫ ሲቸገር
ሌላው ደግሞ ከፍቶት የሚበላው አጥቶ
ሲያንቀጠቅጠው ብርዱ ውስጡ ገብቶ
ሲፈራረቁበት ዝናብና ፀሐይ
እያለኝ ካለፍኩበት እኔም ዓይኔ ሲያይ
አዝማች · Chorus
ይህ ልቤን ተው በለው (፫x)
ይህ ልቤን ተው በለው (፪x)
ምከረው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ልቤን ፈውሰው
ልቤን እጠበው
ልቤን ቀይረው
ልቤን ልብ አርገው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ