የማይተመን ነው በዋጋ
Yemaytemen New Bewaga
2013 · ትራክ 3 · 4:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የዘላለም አምላክ መኖሪያዬ
የሕይወቴ ንጉሥ አለኝታዬ
በከበረው ደምህ የቀደስከኝ
የመንግሥትህ ወራሽ ያረከኝ
የኃጢአት እዳዬን ከፍለህ
መተላለፌንም ደምስሰህ
ማለፍ ሆኖልኛል በደምህ
ክብር ምሥጋና ይሁንልህ
አዝማች · Chorus
የማይተመን ነው በዋጋ
ያገኘሁት ኢየሱስ አንተ ጋ
እኔ አልሄድም ገፍቼህ ለፍቅር
አይገርመኝም የቀረው ይቅር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መሸ ነጋ ሳልል ዘወትር
ቅኔን እቀኛለሁ ለአንተ ክብር
ማልጄ ስነሳ ምሕረትህ
በሌት አዜማለሁ እውነትህን
ስለ እኔ የዋልከው ውለታ
ያረክልኝ ሁሉ ኢየሱስ ጌታ
ተጽፎ ይኖራል በልቤ
ሊጠፋ አይችልም ከሃሳቤ
አዝማች · Chorus
የማይተመን ነው በዋጋ
ያገኘሁት ኢየሱስ አንተ ጋ
እኔ አልሄድም ገፍቼህ ለፍቅር
አይገርመኝም የቀረው ይቅር (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ረክቻለሁ አርፌያለሁ
ረክቻለሁ ወደኸኛልና
ረክቻለሁ አርፌያለሁ
ረክቻለሁ በልጠህብኛልና
አዝማች · Chorus
የማይተመን ነው በዋጋ
ያገኘሁት ኢየሱስ አንተ ጋ
እኔ አልሄድም ገፍቼህ ለፍቅር
አይገርመኝም የቀረው ይቅር
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔ አልሄድም ገፍቼህ ለፍቅር
አይገርመኝም የቀረው ይቅር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ