የመስቀል ፍቅርህ
Yemeskel Fekereh
2008 · ትራክ 1 · 4:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለ ሁኔታዎች ሳዝን ሲከፋኝ
የመስቀል ፍቅርህ ወዳጄ ትዝ እያለኝ
ሚደርስብኝ መከራ እንደ ብዙ ደስታ ቆጠርኩኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ውለታህ መዘነብኝ (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ግራ ሲገባኝ ጭልም ሲልብኝ
ወዲያው መልሶ ፍቅርህ ትውስ ሲለኝ
ነገሩን ትውት አድርጌው ጸልያለሁ/ዘምራለሁ
የታላቅነትህን ሚስጥር አስተውላለሁ
የታላቅነትህን ሚስጥር አስተውላለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታን ለማስከበር ከፍሎ የለ ዋጋ
አንዱ በመጋዝ ሲሰነጠቅ ሌላው በጦር ሲወጋ
አንበሳ ሲበላ ሲጠበስ በዘይት
በድንጋይ ሲወገር ሲቃጠል በእሳት (፪x)
አዝማች · Chorus
አያሳስበኝም መከራ ችግሩ
አያስጨንቀኝም ውርጭና ሀሩሩ
የጌታዬ ሥም ግን በዚም በዚያም መክበሩ
ቁጥር 5 · Verse 5
እሱ ነው ቁም ነገሩ (፬x)
አዝማች · Chorus
አያሳስበኝም መከራ ችግሩ
አያስጨንቀኝም ውርጭና ሀሩሩ
የጌታዬ ሥም ግን በዚም በዚያም መክበሩ
ቁጥር 6 · Verse 6
እሱ ነው ቁም ነገሩ (፲፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ