የእኔ ዓለሜ
Yene Aleme
2019 · ትራክ 1 · 6:36 · አማርኛ
የእኔ ደስታ ኢየሱስ አሃ
የእኔ ዓለሜ የአንተ ክብር ነው /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ መንፈስ ነው /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ ክብር ነው /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ መንፈስ ነው /2/
የሰው ልጅ ምኞቱ ከፍታ ስኬቱ
በመደረግ ያልፋል ሁሉም ነገር ከንቱ
ሕይወት ተገለጠ ለእኔም በርቶልኛል
ኢየሱስ አንተ ነህ ሌላ ምን ያሻኛል
ከአንተ ሌላ አያምረኝም /2/
ከአንተ ውጪ አያምረኝም /2/
ናፍቆቴ ነህ ምኞቴ ነህ
ጉጉቴ ነህ ሕይወቴ ነህ
የለም እንዳንተ ምወደው
የለም እንዳንተ ምናፍቀው
የለም እንዳንተ ምወደው
የለም እንዳንተ ምናፍቀው
በመንፈስ የሆነ ሰላም የሞላው
ሃዘን የሌለበት የአንተ ዓለም ነው
ዳግመኛ ብፈጠር እድሉን ባገኝ
ኢየሱስ አንተ ነህ የምታጓጓኝ
ከአንተ ሌላ አያምረኝም /2/
ከአንተ ውጪ አያምረኝም /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ ክብር ነው /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ መንፈስ ነው /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ ክብር ነው /2/
የእኔ ዓለሜ የአንተ መንፈስ ነው /2/
አንተ ነህ ሰላም አንተ ነህ
(የዚህ ቤት ሰላም የዚህ በቤት ክብር)
ኢየሱስ (ኦሆሆ ሃሌሉያ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ